አዲስ አበባ፣ ኢትዮጵያ
ዋና መስሪያ ቤት: +251 11 666 3339
የሽያጭ ጥያቄ: +251 977 29 29 29
[email protected]
Sell Featured
ሳርቤት ካናዳ ኤምባሲ
ግንባታው በመፋጠን ላይ ያለው ይህ ዘመናዊ የቅንጦት አፓርታማ፣ በታዋቂው የሳርቤት ካናዳ ኤምባሲ አካባቢ ይገኛል። በ 850 ካሬ ሜትር ላይ ያረፈው ግንባታ፣ ወደር የለሽ ቅንጦትን ለርሶ ለማቅረብ በጥንቃቄ በመገንባት ላይ ይገኛል።
እያንዳንዱ አፓርተማ በታላቅ ጥንቃቄ የተነደፈ ሲሆን ከፍተኛ ጥራት ባለቸው ከውጭ በምናስመጣቸው የፊኒሺንግ ቁሳቁሶች የሚሠራ ነው ፣ ይህም በማንኛውም ጊዜ የቅንጦት ሂወትን የሚያንፀባርቅና ጊዜ የማይሽረው ውበትን ያረጋግጣል።
ጂምናዚየም፣ አውቶማቲክ ጀነሬተር እና የተማከለ የሳተላይት ስርዓትን ጨምሮ በዘመናዊ መገልገያዎች ይደሰቱ። የእሳት ማንቂያዎች፣ የጢስ ጠቋሚዎች፣ የCCTV ካሜራዎች እና የ24/7 የደህንነት ሰራተኞች ከሁሉ በላይ የሆነውን ደህንነቶን ያስጠብቃሉ፣ እርሶ የሰላም እንቅልፎን ይተኙ!
ሁለት የግልዎ የመኪና ማቆሚያ ቦታዎች ስላሎት፣ የመኪና ማቆሚያ ቦታ በጭራሽ አያሳስብዎ። በተጨማሪም፣ በአንድ ወለል አራት ቤቶች ብቻ ስላሉ፣ ከፍ ባለ ነጻነት ገለል ብለው የቅንጦት ኑሮዎን መምራት ይችላሉ።
በሰፊ የመኖሪያ እና የመመገቢያ ስፍራዎቾ ዘና ይበሉ ፣ ወይም ለሰላማዊ ሌሊት እንቅልፍ ወደ ምቹ መኝታ ቤቶ ይግቡ። ዘመናዊው እና ሙሉ በሙሉ ፈርኒሽ የተደረገው ኪችን ለምግብ አድናቂዎች ምርጥ ነው ፣ ሰፊው በረንዳ አስደናቂ እይታዎችን እና ከቤት ውጭ የመዝናኛ ቦታን ይሰጣል።
የገቢያ ማዕከላትን፣ ሬስቶራንቶችን እና የመዝናኛ ቦታዎችን ጨምሮ ከቅንጡ አገልግሎቶች አጠገብ የሚገኘው ሳርቤት ካናዳ የቅንጦት አፓርተማዎች ወደር የለሽ ምቾት እና ቅንጡ አኗኗር ይሰጣል።
የቅንጦት ኑሮን በግሩም ሁኔታ የማጣጣም እድል እንዳያመልጥዎ። ዛሬውኑ ቦታዎን ያስይዙ እና የሳርቤት ካናዳ የቅንጦት አፓርታማዎችን አዲሱ ቤትዎ ያድርጉት።