fbpx
Previous Next

2 አዳዲስ የቅንጡ አፓርትመንት ፕሮጀክቶች ከሪያሊቲ ሪል ስቴት

መልካም ዜና! አሁን ከኛ 2 አዳዲስ እና አጓጊ የቅንጡ አፓርትመንት ፕሮጀክቶችን መጠበቅ ይችላሉ። አንዱ ፕሮጀክት ዝግጅቱን አጠናቆ በቦሌ ደምበል አካባቢ፣ አዲስ አበባ፣ ኢትዮጵያ ለመጀመር ጥቂት ነገሮች ብቻ ናቸው የቀሩት። የፕሮጀክቱ ስም ዲፕሎማት ሮድ ፕሮጀክት ሲሆን በ2016 ዓ.ም. ይጠናቀቃል ተብሎ ይጠበቃል።

ልክ እንደ ሌሎቹ የቅንጡ አፓርትመንት ህንፃዎቻችን ጥራት ባላቸው የፊኒሺንግ ግብዓቶች በጥራት ይገነባል። ህንፃው በውስጡ 60 አፓርትመንቶች ሲኖሩት በተለያየ የመኝታ እና የመታጠቢያ ቤት ብዛት ይቀርባል። ከዚህ በተጨማሪም ሌሎች የቅንጡ ተጓዳኝ ነገሮች ማለትም እንደ የመሬት ስር የመኪና ማቆሚያ፣ ድግስ መደገሻ ቦታ፣ ጂም እና ሌሎችም ይኖሩታል።

ሌላኛው የወደፊት ፕሮጀክታችን የሚገነባው ብስራተ ገብርኤል አካባቢ ነው፤ ሌላ የከተማዋ ለመኖሪያ ምቹ እና ሰላማዊ የሆነ ቦታ። በዛ ላይ የኛ ቅንጡ አፓርትመንቶች ሲጨመሩ የበለጠ ለመኖሪያ ምቹ ያደርጉታል። የዚህን ፕሮጀክት ተጨማሪ መረጃዎች ስናጋራ እንዲደርስዎ ድህረገፃችንን ይከታተሉ።

Previous Next

ሪያሊቲ ሪል ስቴት የቦሌ አትላስ የቅንጡ አፓርትመትን ፕሮጀክቱን አጠናቆ አስረክቧል

በታህሳስ 15 ቀን 2014 ዓ.ም. ሪያሊቲ ሪል ስቴት የቦሌ አትላስ ፕሮጀክትን መዝጊያ እና ማስረከቢያ ትልቅ የአከባበር ስነስርዓት አድርጎ ነበር።

በተዘጋጀውም የምሳ ፕሮግራም ላይ የድርጀቱ ዋና ስራ አስኪያጅ፣ የፕሮጀክቱ የመጀመሪያ አፓርትመንት ገዢ እና ሊሎች ደስተኛ የሆኑ የቤት ባለቤቶች ንግግር አድርገዋል። ከዚህ በተጨማሪ የድርጅቱ ጥሩ ውጤት ያስመዘገቡ ሰራተኞች በመድረክ ላይ ሽልማት ተበርክቶላቸዋል እናም በአዲሶቹ የቤት ባለቤቶች እና በሪል ስቴቱ መካከል የቤት ርክክብ ስነስርዓት ተካሂዷል።

ቦሌ አትላስ የድርጅቱ ስኬታማ እና ዋና የሚባል ፕሮጀክት ነው። ፕሮጀክቱ ከጥራት በተጨማሪ ከታቀደለት ጊዜ ቀደም ብሎ ለገዢዎች ተረክቧል። ህንፃው ባለ 10 ፎቅ ሲሆን ለመጠናቀቅም 2 አመት ብቻ ፈጅቶበታል፣ የሚገኝውም ቦሌ አትላስ አካባቢ ነው። በአንድ ፎቅ ውስጥ 3 አፓርትመንቶች የገኛሉ፤ ከዚህም በተጨማሪ ህንፃው ውስጥ ጂም፣ የመሬት ስር የመኪና ማቆሚያ፣ ድግስ/ፕሮግራም ማዘጋጃ ቦታ፣ አውቶማቲክ ጄነሬተር፣ አሳንሰር እና ሌሎችም አጓጊ ነገሮች አብረውት መጥተዋል።

የፕሮጀክት መዝጊያ እና ማስረከቢያ የምሳ ፕሮግራሙ የተካሄደው ራሱ ህንፃ ውስጥ ሲሆን የአፓርትመቶቹ ባለቤቶች፣ የድርጅቱ ሰራተኞች እና ሌሎች ተጋባዥ እንግዶች ተገኝተዋል። ኢቢኤስ ቲቪም በቦታው ተገኝቶ ፕሮግራሙን ቀርፆ ኢትዮ ቢዝነስ ሾው ላይ አሳይቷል።

ቦሌ ብራስ፣ ዩጎ ቤተክርስቲያን አጠገብ
አዲስ አበባ፣ ኢትዮጵያ
ዋና መስሪያ ቤት: +251 11 666 3339
የሽያጭ ጥያቄ: +251 977 29 29 29
[email protected]

በኢሜይሎ መረጃ እንዲደርስዎ

ማህበራዊ ድረገፆቻችን ይከታተሉ