በታህሳስ 15 ቀን 2014 ዓ.ም. ሪያሊቲ ሪል ስቴት የቦሌ አትላስ ፕሮጀክትን መዝጊያ እና ማስረከቢያ ትልቅ የአከባበር ስነስርዓት አድርጎ ነበር።
በተዘጋጀውም የምሳ ፕሮግራም ላይ የድርጀቱ ዋና ስራ አስኪያጅ፣ የፕሮጀክቱ የመጀመሪያ አፓርትመንት ገዢ እና ሊሎች ደስተኛ የሆኑ የቤት ባለቤቶች ንግግር አድርገዋል። ከዚህ በተጨማሪ የድርጅቱ ጥሩ ውጤት ያስመዘገቡ ሰራተኞች በመድረክ ላይ ሽልማት ተበርክቶላቸዋል እናም በአዲሶቹ የቤት ባለቤቶች እና በሪል ስቴቱ መካከል የቤት ርክክብ ስነስርዓት ተካሂዷል።
ቦሌ አትላስ የድርጅቱ ስኬታማ እና ዋና የሚባል ፕሮጀክት ነው። ፕሮጀክቱ ከጥራት በተጨማሪ ከታቀደለት ጊዜ ቀደም ብሎ ለገዢዎች ተረክቧል። ህንፃው ባለ 10 ፎቅ ሲሆን ለመጠናቀቅም 2 አመት ብቻ ፈጅቶበታል፣ የሚገኝውም ቦሌ አትላስ አካባቢ ነው። በአንድ ፎቅ ውስጥ 3 አፓርትመንቶች የገኛሉ፤ ከዚህም በተጨማሪ ህንፃው ውስጥ ጂም፣ የመሬት ስር የመኪና ማቆሚያ፣ ድግስ/ፕሮግራም ማዘጋጃ ቦታ፣ አውቶማቲክ ጄነሬተር፣ አሳንሰር እና ሌሎችም አጓጊ ነገሮች አብረውት መጥተዋል።
የፕሮጀክት መዝጊያ እና ማስረከቢያ የምሳ ፕሮግራሙ የተካሄደው ራሱ ህንፃ ውስጥ ሲሆን የአፓርትመቶቹ ባለቤቶች፣ የድርጅቱ ሰራተኞች እና ሌሎች ተጋባዥ እንግዶች ተገኝተዋል። ኢቢኤስ ቲቪም በቦታው ተገኝቶ ፕሮግራሙን ቀርፆ ኢትዮ ቢዝነስ ሾው ላይ አሳይቷል።