መልካም ዜና! አሁን ከኛ 2 አዳዲስ እና አጓጊ የቅንጡ አፓርትመንት ፕሮጀክቶችን መጠበቅ ይችላሉ። አንዱ ፕሮጀክት ዝግጅቱን አጠናቆ በቦሌ ደምበል አካባቢ፣ አዲስ አበባ፣ ኢትዮጵያ ለመጀመር ጥቂት ነገሮች ብቻ ናቸው የቀሩት። የፕሮጀክቱ ስም ዲፕሎማት ሮድ ፕሮጀክት ሲሆን በ2016 ዓ.ም. ይጠናቀቃል ተብሎ ይጠበቃል።
ልክ እንደ ሌሎቹ የቅንጡ አፓርትመንት ህንፃዎቻችን ጥራት ባላቸው የፊኒሺንግ ግብዓቶች በጥራት ይገነባል። ህንፃው በውስጡ 60 አፓርትመንቶች ሲኖሩት በተለያየ የመኝታ እና የመታጠቢያ ቤት ብዛት ይቀርባል። ከዚህ በተጨማሪም ሌሎች የቅንጡ ተጓዳኝ ነገሮች ማለትም እንደ የመሬት ስር የመኪና ማቆሚያ፣ ድግስ መደገሻ ቦታ፣ ጂም እና ሌሎችም ይኖሩታል።
ሌላኛው የወደፊት ፕሮጀክታችን የሚገነባው ብስራተ ገብርኤል አካባቢ ነው፤ ሌላ የከተማዋ ለመኖሪያ ምቹ እና ሰላማዊ የሆነ ቦታ። በዛ ላይ የኛ ቅንጡ አፓርትመንቶች ሲጨመሩ የበለጠ ለመኖሪያ ምቹ ያደርጉታል። የዚህን ፕሮጀክት ተጨማሪ መረጃዎች ስናጋራ እንዲደርስዎ ድህረገፃችንን ይከታተሉ።